Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት 62 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ምግብ ነክ ድጋፍ ይፈልጋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ችግር ባስከተለው ተፅዕኖ 62 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ምግብ ነክ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በክልሉ በፀጥታ ችግር ከቀያቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን የተለያየ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ታረቀኝ ቴሲሳ ገልጸዋል፡፡

በከማሺ ዞን እስካሁን ባለው የፀጥታ ችግር በሁሉም ቦታዎች ሰብዓዊ ድጋፍ በሚፈለገው ልክ ተደራሽ አለመሆኑን ጠቁመው፥ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ከ384 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አስፈላጊ ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

አንፀራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተሰሩ እንደሆነም ኮሚሽነሩ መናገራቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

በተያዘው የመኸር ምርት ዘመን መሰብሰብ የነበረበት ሰብል በሚፈለገው ልክ ባለመሰብሰቡ ምክንያት÷ የምግብ እህል ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንም ኮሚሽነር ታረቀኝ ቴሲሳ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.