Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ከቱሪዝም ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን በደሴ ከተማ እያከናወነ ነው።

በግምገማው ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ እንዳሉት፥ የክልሉ የቱሪዝም መስክ ባለፋት ስድስት ወራት በጦርነትና በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ጉዳት ደርሶበታል።

በመሆኑም በሚቀጥሉት ወራት የቱሪዝም ሐብቶችን በማስተዋወቅ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ጎብኝዎች በጥቅሉ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን ነው ያመለከቱት።

በሌላ በኩል የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘምም ወደ ሥራ ተገብቷል ነው የተባለው።

በተያዘው ዕቅድ መሰረት በሚቀጥሉት 6 ወራት ከሃገር ውስጥና ከውጭ ከ3 ሚሊየን በላይ ጎብኝዎች ወደ ክልሉ እንዲመጡ እየተሰራ ነው።

ለዚህም እንዲያግዝ መስህቦችን የማስተዋወቅ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው ተግልጿል፡፡

በሙሉቀን አበበ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.