የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጋራ ምክክር መድረክ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አጎራባች ወረዳዎች የአመራሮችና የጸጥታ ተቋማት የጋራ ምክክር መድረክ በሽዋሮቢት ከተማ መካሄድ ጀመረ።
የምክክር መድረኩ ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች አሁን ላይ ያገኙትን ሰላምና አብሮነትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረጻዲቅ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የህዝብ ለህዝብ መድረኮች ይፈጠራሉ ነው ያሉት።
የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው፥ በሁለቱ ዞን አመራሮችና ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን አንድነትና ሰላም ለማስቀጠል በጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል።
የጋራ መድረኩ የቀጠለ ሲሆን÷ ውይይቱ በሁለቱ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች እየተመራ ነው።
በግርማ ነሲቡ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!