Fana: At a Speed of Life!

ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም የወጪ ንግድ 658 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም የወጪ ንግድ 658 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ፡፡

ባለፉት ሰባት ወራት 145 ሺህ 321 ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 461 ነጥብ 81 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን÷ 169 ሺህ 748 ቶን በመላክ 658 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡

አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 58 ሺህ 385 ቶን በገቢ ደግሞ 302 ነጥብ 51 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን ከቡና እና ሻይ ባለስጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.