የሀገር ውስጥ ዜና

ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም የወጪ ንግድ 658 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

By Feven Bishaw

February 16, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም የወጪ ንግድ 658 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ፡፡

ባለፉት ሰባት ወራት 145 ሺህ 321 ቶን የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 461 ነጥብ 81 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን÷ 169 ሺህ 748 ቶን በመላክ 658 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡