Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተከሰተ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በትናትናው እለት በተከሰተው የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
የአዲስ አበባ አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ በመዲናዋ በትናንትናው ዕለት ሁለት የእሳት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡
አንዱ የእሳት አደጋ ትናንት 11 ሰዓት ከ50 ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 5 በመኖሪያ ቤት ላይ የደረሰ ሲሆን ÷ 100 ሺህ ብር የሚገመት የንብረት ውድመት አድርሷል፡፡
ኮሚሽኑ ጥሪ እንደረሰው የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎችን እና ሠራተኞችን ወደ ቦታው መላኩን የገለፁት ባለሙያው፥ በዚህም አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም 200 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ገልፀው የሰው ሕይወት ላይም ጉዳት አለመድረሱን አመላክተዋል።
ሌላኛው የእሳት አደጋ ከምሽቱ 8 ሰዓት ከ 42 ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በአራት የንግድ ሱቆችና በአንድ ፔኒሲዮን ላይ የደረሰ ነው ብለዋል፡፡
በአደጋው በፔኒሲዮኑ አልጋ ተከራይተው የነበሩ 2 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፥ 200 ሺህ ብር የሚገመት ንብረትም ወድሟል።
በተደረገው ርብርብ 3 ሰዎችን እንዲሁም 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ነው ባለሙያው የተናገሩት፡፡
የአደጋዎቹ መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
አቶ ንጋቱ ማሞ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት ለሚሰጡት ማህበረሰቦች ከመሰል አደጋዎች እንዲጠበቁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉናተገልጋዮችም አካባቢውን ማጣራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
እንዲሁም የአየር ፀባዩ ፀሐያማና ነፋሻማ በመሆኑና ለእሳት አደጋ መባባስ አስተዋፅኦ የሚያደርግ በመሆኑ ነዋሪው ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደረግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በፌቨን ቢሻው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.