Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል ድህነትን ለመቀነስና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ድህነትን ለመቀነስና እና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በክልሉ ሁለተኛው ዙር የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በይፋ የተጀመረ ሲሆን÷ በመድረኩ ላይ ተገኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፥ ስር የሰደደ ድህነትን ለመቀነስ እና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በጥራት ማከናወን ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዋና አላማም በተለይ የህብረተሰቡን ህይወት መቀየር መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቆጥበው ወደ ጥቃቅንና አነስተኛ ለሚሸጋገሩ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሁለተኛው የከተማ ሴፍቲኔት መርሃግብር ቀደም ሲል የታዩ ክፍተቶቸን በማረምና ጥንካሬዎችን በማጎልበት በትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሁለተኛው ዙር የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም 1 ሺህ 562 ዜጎች ተጠቃሚ ያደርገ የልማት ስራ ለማከናወን አስፈላጊውን የልየታና ሌሎች ስራዎች መጠናቀቃቸው የተመላከተ ሲሆን ÷በመርሃግብሩም በአረንጓዴ ልማት፣ በደረቅ ቆሻሻ እና ሌሎች ተግባራት እንደሚከናወኑ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.