Fana: At a Speed of Life!

አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሦስት ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላገለች።
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ወልዴ ቡቃቶ፤ እናቲት በሆስፒታሉ በቂ የቅድመ ወልድ ህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩ ገልጸዋል።
በዚህም ዛሬ ረፋዱ ሦስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሦስት ልጆች በሰላም መገላገላቸውን አስታውቀዋል።
ወላዷ እናት በሰላም እንዲገላገሉ የህክምና ባለሙያዎች ላደረጉት ደጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ህፃናቱ የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ ባይሆንም ከሚጠበቀው ክብደት በታች በመሆናቸው ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ልዩ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና መወሰዳቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ የጊዶ ቦዲቲ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ብርሃነሽ ቆልቻ ከዚህ በፊት የወለዷቸው ሦስት ሴት ልጆች እንዳሏቸውም ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.