Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ተቋም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ተቋም ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ተቋም ጋር ያላትን ትብብር ስለ ማጠናከር መክረዋል፡፡

ውይይታቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷”ከክሪስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ተቋም ጋር ያላትን ትብብር ስለ ማጠናከር እና የለውጡን ሂደት በቀጣይነት ስለ መደገፍ ተወያይተናል” ብለዋል።

የአውሮፓ ኅብረት – አፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ዛሬ በብራሰልስ ይጀምራል፡፡
ጉባዔው ዛሬ እና ነገ እንደሚካሄድ እና የሁለቱ ህብረቶች አባል ሀገራት መሪዎች ይካፈሉበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ጉባኤ ላይ ለመታደም በትናትናው እለት ብራስልስ መግባታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.