Fana: At a Speed of Life!

ጉባዔው የትብብርና የአጋርነት ሥራዎችን ለማጠናከር የሚያስችል ግብዓት እንደሚያስገኝልን እምነቴ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት እና የአውሮፓ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሁለቱ አኅጉራት መካከል ያሉትን ወቅታዊ እና ቀጣይ የትብብር እና የአጋርነት ሥራዎች ለማጠናከርና ዘላቂ ለውጥን ለማምጣት የሚያስችል ግብዓት እንደሚያስገኝልን እምነቴ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
6ኛው የአውሮፓ ኅብረት – አፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በቤልጂየም ብራሰልስ ተጀምሯል፡፡
በጉባኤው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ለዚህ ተፈጻሚነት ኢትዮጵያም እንደ ቀደምት የአፍሪካ ኅብረት መሥራች ሀገር የበኩሏን ሚና ትጫወታለች ብለዋል።
ጉባዔው ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ሲሆን፥ የሁለቱ ኅብረቶች አባል ሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ነው፡፡
በጉባዔው መሪዎቹ የላቀ ብልጽግና እውን ለማድረግ በምን መልኩ መሥራት እንዳለባቸው የሚያመላክቱ ሀሳቦችና በጸጥታና ደኅንነት ላይ ባሏቸው ምልከታዎች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች እና በሚነሱት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እውቀቱ ያላቸው ተጋባዥ ምሁራን እንደሚሳተፉ እና ሙያዊ ምልከታቸውንና የመፍትሄ ሃሳቦቻቸውን እንደሚያቀርቡ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት በመረጃው ይፋ አድርጓል፡፡
የአውሮፓ ኅብረት- አፍሪካ ኅብረት የ2030 የጋራ ራዕይ መግለጫ በተሳታፊዎች ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.