ስፓርት

የኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ እና የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድን የክስ ሂደት እልባት አገኘ

By Feven Bishaw

February 17, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ እና በሲዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድን መካከል ሲደረግ የነበረው የዲሲፕሊን ክስ ሂደት እልባት አግኝቷል፡፡

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በኅዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ከማድረጋቸው አንድ ቀን አስቀድሞ የሲዳማ ቡና ክለብ ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር እና ሥነ ስርዓት ኮሚቴ ባስገባው ደብዳቤ የዕለቱ ዳኛ በዓምላክ ተሰማ ‘የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ በመሆናቸው ጨዋታውን በዳኝነት እንዳይመሩ’ በሚል ቅሬታ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።