የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ፍሪያማ ውይይት አካሄዱ

By Feven Bishaw

February 17, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡

ውይይቱን አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ “ከወንድሜ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና አኅጉራዊ ጉዳዮች ላይ ስለ ነበረን ፍሬያማ ውይይት ምስጋናዬ ይድረስ” ብለዋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቤልጂየም ብራሰልስ እየተካሄደ በሚገኘው 6ኛው የአውሮፓ ኅብረት እና አፍሪካ ኅብረት የጋራ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡