የኢትዮ – ኬንያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ዘርፉ መሥፋት አለበት – አምባሳደር መለስ ዓለም
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ከኬንያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ሥራ አሥፈጻሚ ሳሙኤል ማቶንዳ እና ከንግዱ ዘርፍ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በወይይታቸውም÷ ኢትዮጵያና ኬንያ በበርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና የንግድ ግንኙነቶች ላይ በትብብር ሊሰሩ በሚችሉባቸው አማራጮች ላይ ከሥራ አስፈጻሚው እና እርሳቸው ከመሩት ልዑካን ቡድን ጋር መክረዋል፡፡
አምባሳደር መለስ ዓለም ÷ የኢትዮጵያ እና የኬንያ ንግድ ምክር ቤቶች በጥምረት ሊሠሩባቸው በሚችሉበት ዘርፍ ላይ እና በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ እና ለማመጣጠን የሚያስችሉ አዲስ እይታዎችን ያመላከተ ውይይት ማድረጋቸውንም ነው የገለጹት፡፡
በውይይቱም ላይ ሁለቱ ሀገራት በዲፕሎማሲያዊ መስክ የገነቡትን ግንኙነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ዘርፉ ሊያሰፉት እንደሚገባ ነው አምባሳደር መለስ ዓለም ያነሱት።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!