ዓለም ባንክ ለሶማሌ ክልል 64 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ባንክ በሶማሌ ክልል ለተከሰተው ድርቅ አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ 64 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መመደቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።
ክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ ከተመደበው ድጋፍ ውስጥ 38 ሚሊየን ዶላሩ አሁን የሚሰጥ መሆኑን አቶ ሙስጠፌ ገልጸው÷ የዓለም ባንክ ላደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!