Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ዋና ኃላፊ ህወሓት በደቡብ ወሎ ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (ዩ ኤን ዲ ፒ) ዋና ኃላፊ ቱርሃን ሳልህና ሌሎች የልማት ድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ያደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ።
ዋና ኃላፊው ቱርሃን ሳልህና ምክትል ኃላፊው ክሊዎፋስ ቶሮሪን ጨምሮ በጉብኝቱ ለተሳተፉ የልማት ድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴንና ሌሎች አመራሮች ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን፥ ወራሪው ቡድን እስካሁን በተደረገ የመረጃ ማሰባሰብ ሥራ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸሙን እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳዊ ውድመት ማድረሱን አብራርተዋል፡፡
ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው፥ በርካቶች የሥነ ልቦና ጉዳትና ጫና እንዲደርስባቸው መደረጉን ጠቁመው፥ ተቋማት ለኀብረተሰቡ መስጠት በሚገባቸው አገልግሎት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም ነው የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.