Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ያዘጋጀው ሦስተኛው ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ያዘጋጀው ሦስተኛው ጉባኤ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።
 
ጉባኤው የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ የአማራ ሕዝብ ተጨባጭ ተግዳሮቶች እና ተግባራዊ አቅጣጫዎች ዙርያ እንደሚመክር ተገልጿል፡፡
 
በዚህ ጉባኤ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ፣ የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.