Fana: At a Speed of Life!

የቡርጂ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡርጂ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (ወናንካ አያና) በዓል ለ2ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው፡፡

የወናንካ አያና ክብረበዓል አጎራባች ከሚገኙ ብሔረሰቦች ጋር ለሚኖር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚያበርከት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዓሉን አስመልክቶ የሲምፖዚየም ውይይትም የተካሄ ሲሆን፥ በኬንያ የማርሳቤት ካውንቲ ምክትል አስተዳዳሪና የብሔረሰቡ ተወላጅ የሆኑት ሰለሞን ጎቤ ማንነትን በአዎንታዊ መልኩ ለማሳደግና ሌሎች የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ምሁራን ከመንግስት ጋር ተቀራርበው መምከራቸው የሚደነቅና ሊጠናከር የሚገባው መሆኑን ተናግሯል፡፡

የሲምፖዚየም ውይይቱ በመሠረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች ዙሪያ ጥናት በማካሄድና የመፍትኄ አቅጣጫዎችን በመጠቆም የሚጠበቅበትን ይወጣል ያሉት ደግሞ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ገጠር ልማትና ግብርና ኤክስቴንሽን ትምህርት ክፍል መምህርና የምሁራን መማክርት ጉባኤ ሰብሳቢ ረዳት ፕሮፌሰር ዮሐንስ ማሬ ናቸው፡፡

የወናንካ አያና በዓልን ለመታደም በመብቃታቸው ደስተኛ መሆናቸውን የተናገሩት ተወላጆቹ፥ በዓሉ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ተወላጆችንና ወዳጆችን የሚያሰባስብ በመሆኑ ልዩ ስሜት የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

በዓሉ እሴቱን ጠብቆ ከተለያዩ አካባቢዎች በመጡ ተወላጆችና ወዳጆች በድምቀት እየተከበረ መሆኑን ከድሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.