Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩንቨርስቲ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩንቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 135 ተማሪዎችን አስመረቀ።

የተመረቁት ተማሪዎች በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በርቀትና ተከታታይ መርሀ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

ከተማሪዎቹ መካከል 2 ሺህ 440 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 699 በሁለተኛ ዲግሪና ስምንቱ ደግሞ በሶስተኛ ድግሪ የተመረቁ ሲሆኑ፥ 237 ተመራቂዎች የህክምና ዶክተሮች ናቸው።

በተጨማሪም ከሶማሌ ላንድ ሪፐብሊክና ከሩዋንዳ ትምህርታቸውን በጅማ ዩኒቨርስቲ ሲከታተሉ የነበሩ 13 ተማሪዎች ዛሬ ተመርቀዋል።

የምረቃ ስነስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ ለተመራቂ ተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ተመራቂዎች የቀሰሙትን እውቀት በተግባር በማዋል የሀገሪቷን እድገት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያርጉም ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የጅማ ዩኒቨርስቲ በመደበኛ፣ በማታ፣ በክረምት፣ በርቀትና ተከታይ የትምህርት መርሀ ግብር ከ47 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

በሙክታር ጠሀ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.