Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሀረርጌ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የምግብ እህል ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ሁለት ወረዳዎች ከ2 ሺህ 200 ኩንታል በላይ የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ አደጋ ስጋት አመራርና ልማት ተነሺዎች ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ አልፊያ አልዪ እንዳሉት ÷ በዞኑ ሀዊ ጉዲና እና ቡርቃ ዲምቱ ወረዳዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የተደረገው ድጋፍ ከዞኑና ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች የተሰበሰበ ነው።

ከዚህም ባሻገር በሁለቱ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ያጋጠመውን የውሃ ችግር ለማቃለል እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ 11 ቦቴ ውሃ መቅረቡን ገልጸዋል።

ሀዊ ጉዲና እና ቡርቃ ዲምቱ ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ቆላማ አካባቢዎች በመሆናቸው ለድርቅ ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ስለሆነ ቀጣይ ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

ጉምቢ ቦርደዴ፣ ሚኤሶና ኦዳቡልቱም ወረዳዎች ከፊል ቆላማ የአየር ንብረት ያላቸው በመሆኑ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ ከበደ እንዳሉት ከየቦታው ተሰብስቦ በሚሰጥ ድጋፍ ብቻ ችግሩን ማቃለል እንደማይቻል ጠቁመው፤ የመስኖን ልማትን በማጠናከር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል።

አርሶ አደሩ በሰባት ወር በሚደርሰው ማሽላ ላይ ከማተኮር ይልቅ በሦስት እና በአራት ወር በሚደርሱ እንደ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ማሾ የመሳሰሉ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አነስተኛ ግድቦችን በማስፋፋት በዞኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ለድርቅ ተጋላጭነትን በ80 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን ምክትል አስተዳዳሪው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.