Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ ሆስፒታል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የእንያት ሆስፒታል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትሯ ተወካይ ዶክተር አባስ ሁሴን፥ በኢትዮጵያ ላለፉት አመታት መከላከልን ማዕከል ባደረገ፣ ሕክምናን ለማሻሻልና ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት መደረጉንና በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ነው የገለፁት።

ነገር ግን ከማህበረሰቡ በተለያዩ ጊዜያት የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን በተመለከተ ቅሬታ እያሰማ እንደነበር ያነሱት ዶክተር አባስ፥ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎች መገንባትና አገልግሎት መስጠት ለቅሬታዎች ምላሽ እንደሚሆን ገልፀዋል።

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ፥ የግል ጤና ተቋማት እንዲጠናከሩ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ የተለያየ ደረጃ ያላቸው 800 በላይ የግል የጤና ተቋማት አሉ ነው ያሉት።

የእንያት ሆስፒታል ባለቤትና ስራአስኪያጅ ዶክተር አሸብር መዘነ በበኩላቸው፥ ከተማዋን የሕክምና ቱሪዝም ለማድረግና የተሻለ ሕክምና ፍለጋ የሚደረግ ረዥም ጉዞ ለማስቀረት ያለመ ስራ አቅደው መነሳታቸውን ነው የገለፁት።

በመለሰ ታደለ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.