Fana: At a Speed of Life!

ዓባይ እና የህዳሴ ግድብ ዐበይት ሁነቶች

1922 ፦ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የመጀመሪያውን ጥናት ያካሄደችው በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1922 ዓመተ ምህረት ነበር።
በወቅቱ የብሪታኒያ መንግሥት የዓባይን መነሻ ምንጭ ለማወቅ እና በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ያለመ ቡድን ወደ ዳንግላ ከተማ ልከው ነበር።
1927፦ በ19 27 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በእንግሊዛዊው የምድር አሳሽ ሮበርት ኤርነስት ቺዝ ማን የሚመራ ጥናት ተካሂዷል።
1958፦ 19 58 ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ሌላ ሙከራ ያደረገችበት ነበር። በወቅቱ በ19 27ቱ ጥናት ለግድብ ግንባታ ከተመረጡ በአንዱ ግድብ የመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር። በጊዜው የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከአሜሪካ መንግሥት ጋር በመተባበር በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ያቀዱት ዕቅድ አሁን በብሪታኒያ መንግሥት አደናቃፊነት መክኗል።
2003፦ ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ፤ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ቆርጣ መነሳቷን በተግባር አሳየች። መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ጉባ ላይ ተቀመጠ።
2005፦ ግንቦት 2005 በግድቡ ግንባታ የሥራ ደረጃ ምክንያት የዓባይን ወንዝ አቅጣጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀየረ።
2007፦ መጋቢት 2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል የሶስትዮሽ የመርሆዎች ስምምነት ተፈረመ።
2012፦ ኢትዮጵያ፥ ሀምሌ 2012 ዓ.ም ኢትዮጵያ 4 ነጥብ 5 ቢልየን ሜትር ኪዩብ ውሃ በመሙላት የግድቡን የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌትን አሳካች።
2013፦ ነሃሴ 2013 ዓ.ም 13 ቢልየን ሜትር ኪዩብ የውሃ ሙሌትን ያሳካው ሁለትኛው ዙር ውሃ ሙሌት ተከናወነ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.