ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፖለቲካ መጠቀሚያነት ወጥቶ ወደ ሃይልና ህዝብ መጠቀሚያነት እንዲወርድ ያደረገ አመራር ፈጥሯል-ዶክተር አብርሃም
አዲ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፖለቲካ መጠቀሚያነት ወጥቶ ወደ ሃይልና ህዝብ መጠቀሚያነት እንዲወርድ ያደረገ አመራር መፈጠሩን ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡
ዶክተር አብርሃም በላይ የመከላከያ ሚኒስትርና የግድቡ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የግድቡ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በአመራር እና ትውልድ ቅብብል የቀጠለ እና በአሁኑ ስዓት ለውጤት የበቃ ፕሮጀክት ነው፡፡
ባለፉት ዓመታት ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ውስብስብ ችግሮች ያጋጠሙት ቢሆንም÷ ያ ሁሉ ችግር ተቀርፎ ለዚህ ውጤት ዕንዲበቃ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት በተለይም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት የቅርብ ክትትል ላደረጉት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በሃገራችን በየአመቱ 13 በመቶ እያደገ የመጣውን የሃይል ፍላጎት ለመፍታት ይህ ፕሮጀክት እንደሚፈተናው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!