Fana: At a Speed of Life!

ግድቡ በኃይል አቅርቦቱ በዲፕሎማሲ እና በተለያዩ መስኮች ሁሉን አቀፍ ጥቅም የሚሰጥ ነው- የሳሊኒ ዋና ስራ አስኪያጅ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ) ግድቡ ከኃይል አቅርቦቱ በተጨማሪ በዲፕሎማሲ እና በተለያዩ መስኮች ሁሉን አቀፍ ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን የሳሊኒ ኩባንያ መስራች፣ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ፔድሮ ሳሊኒ ተናገሩ፡፡
ስራ አስኪያጁ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ “ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትሩፋት ይዞ ይመጣል፤ ይህንንም የምለው እኔ እራሴን እንደኢትዮጵያዊ ስለምቆጥር ነው” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከፈጣሪ የተሰጣት ልዩ ጸጋ ውሃ መሆኑን ገልጸው÷ ውሃዋንም ለታዳሽ ኃይል ማመንጫነት ማዋል መቻሏን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሳይታለች ብለዋል፡፡
ግድቡ የቱሪዝም ዘርፎችን በመደገፍ በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ እናዳለውም ነው የጠቆሙት፡፡
ይህ ፕሮጀክት በቀላሉ ለዚህ አልደረሰም ያሉት ፔድሮ ሳሊኒ÷ ግድቡ እንዳይሳካ ጥረት የሚያደርጉ ብዙ ጠላቶች ነበሩ፤ ይህንን ተቋቁመን የመጀመርያውን ውጤት ማየት ስለቻልን በጣም ደስ ብሎኛል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.