Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ የአንድነታችን ተምሳሌት መሆኑን አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ኃይል ማመንጨት የጀመረው የህዳሴ ግድብ የአንድነታችን ተምሳሌት በመሆኑ ከጥላቻና ልዩነት ወጥተን አንድ የምንሆንበት ጊዜ ነው ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ-ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ግድቡ ኢትዮጵያውያንን አንድ የሚያደርግ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ግጭትና እርስበርስ መበላላት ለኢትዮጵያ የሚፈይደው ነገር የለምና ከስህተቶቻችን በመማር የኢትዮጵያን ልማትና እድገት ልናረጋግጥ ይገባል ነው ያሉት።
አቶ ኃይለማሪያም በንግግራቸው ልዩነቶችን እና ቁርሾዎችን በመተው ለአንድነት መስራት አስፈላጊ መሆኑን በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ጊዜ ላይ ለመድረስ በርካታ ውጣውረዶች አልፈዋል ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህም ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.