Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞንና የአፋር አጎራባች ወረዳወች ለሰላምና ለልማት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር እና የአፋር ክልል አጎራባች ወረዳወች የአመራር አካላት አካባቢያቸውን ሠላም በማድረግ ማህበረሰቡን ከድህነት በሚያወጡ የልማት እቅዶች ላይ በጋራ ለመሥራት መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር እና ከአፋር ክልል ሁለት ዞኖች የተውጣጡ አጎራባች ወረዳዎች የተሳተፉበት የልማት፣ የሠላም እና የወንድማማችነት የምክክር መድረክ በባቲ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በተካሄደው መድረክ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን፣ ከአፋር ክልል የሀውሪስ ዞን እና ከአሪረሱ ዞን የተውጣጡ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በአማራ ክልል ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን 5 ወረዳወችና 2 ከተሞች እንዲሁም ከአፋር ክልል ከሁለቱም ዞኖች የሠባት ወረዳወች አመራሮች ናቸው በመድረኩ የተሳተፉት፡፡
በአለባቸው አባተ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.