ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ሥራ በመጀመሩ የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንቷ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ‘‘በንጉሡ ራዕይ ተጀመረ ፤ ድፍረት ተከተለ ፤ አስቀጣዮች መጡ ፤ ግድባችን ኃይል አመነጨ! እንኳን ደስ አለን!’’ ብለዋል፡፡
ሀሩርን ተጋፍጦ ፤ ጤናውን ሕይወቱን ሰዉቶ ፤ የአገርን ጥቅም የሙጥኝ ይዞ ተደራድሮ ፤ ካለው አካፍሎ ፤ አገሬ ብሎ ለተነሳ ሁሉ ቀኑ የእናንተ ነው፤ እጅ እነሳለሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ የሁላችንም ነችና የአገር ጉዳይ ስለሚመለከተን፣ የዜግነት መብትና ግዴታ ስላለን፣ በአገር ጥቅም ላይ ለአፍታም ሳንዘናጋ ከተነጋገርን፣ ከተደማመጥን፣ ከተግባባን፣ ከተከባበርንና ከተባበርን የሚያቅተን ነገር የለም ፥ ከሚያዘናጋን እንራቅም ሲሉም ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!