Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣የካቲት 14፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች የኮሮና ተህዋሲ /ኮቪድ/ ወረርሽኝን በቅንጅት መከላከልና ምላሽ መስጠት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው።

ውይይቱ ስለ ኮቪድ አዳዲስ መረጃዎችን ለመለዋወጥና ወረርሽኙን በአህጉር ደረጃ በቅንጅት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተጠራ አስቸኳይ የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች ጉባዔ ነው ተብሏል።

ሚኒስትሮቹ  በወረርሽኙ ዙሪያ የተቀናጀ አህጉራዊ የመከላከልና ለበሽታው ምላሽ የመስጠት ስትራቴጂ ላይ ስምምነት መድረስ የሚያስችል ውይይት እንደሚያካሄዱ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በቻይና ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ አፍሪካዊያን ተማሪዎችና ዜጎች ወደ አገራቸው መመለስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይም እየመከሩ  መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለበሸታው እየተደረጉ ያሉ የመድሃኒት ምርምሮች፣ ክትባቶችና በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ የልምድና የመረጃ ልውውጥ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ከጄኔቭ በቪዲዮ ኮንፍረንስ በቀጥታ በመድረኩ እየተሳተፋ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፈቂ መሀማት እና የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጉባዔው ላይ  መገኘታቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.