ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነገ ለሕዝብ ተወካዮች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከተወካዮቹ ለሚነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ እንደሚሰጡ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከህዝብ ተወካዮች ለሚነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የሚሰጡትን ማብራሪያ እና ምላሽ በሁሉም የመገናኛ አማራጮቹ በቀጥታ የሚያስተላልፍ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!