በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋርም አፍሪካና ኤስ ኦ ኤስ ሳህል የተሰኙ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በቦረና ዞን አራት ወረዳዎች ለሚገኙ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእንስሳት መኖ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የፋርም አፍሪካ የተግባቦት ስራ አስኪያጅ መድሃኒት ገብረሚካኤል፥ ድርቁ በእንስሳት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ጠቁመው፥ ፋርም አፍሪካ ድርቅን በዘላቂነት ለማስቀረት በተፈጥሮ ሀብት ልማት ላይ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከችግሩ ስፋት አንፃር በቂ አለመሆኑ የተጠቀሰ ሲሆ፥ በተጠናከረ መልኩ ለመደገፍ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው የሚደረጉ እርዳታዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ድጋፉ በቦረና ዞን ለሚገኙ ለሀሬሮ፣ ዳስ፣ ዱብሉቅ እና ዋጭሌ ወረዳዎች የተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡