በቆቦ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከተለያዩ የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ ለተጠለሉ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ድጋፉም የስንዴ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት፣ አተር እና የማዕድ ጨውን ያካተተ መሆኑን ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል፡፡
በተያዘው ሣምንትም ለ12 ሺህ ሰዎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ እና መጠለያ ቁሳቁስ ድጋፍ በመደረግ ላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!