ክፍለ ከተማው በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወዳጅ ኃይለማርያም ለአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን ዛሬ አስረክበዋል።
ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት÷ ለተፈናቀሉ ወገኖች የእለት ደራሽ እርዳታ ማቅረብና መደገፍ ለመንግስት ብቻ የሚተው ጉዳይ ሳይሆን÷ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት እገዛ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም ክፍለ ከተማው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ከ11ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብና አልባሳት ለተጎጂ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው÷ ክፍለ ከተማው ወደፊትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የሽብር ቡድኑ አሁንም በክልሉ በከፈተው ትንኮሳና ወረራ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እየተፈናቀለ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ከዞኑ የተፈናቀሉትን ጨምሮ በክልሉ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ዜጎች በጦርነቱ ሳቢያ የእለት ደራሽ እርዳታ እንደሚያስልጋቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!