Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር በኢስላማባድ ኤምባሲ ልትከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ መሃመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዛሬው ዕለት በፓኪስታን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ከፓኪስታን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም ሀገራቱ በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ በትኩረት መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ፓኪስታን በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለኢትዮጵያ ያሳየችውን አጋርነት እና ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከፍ ባለ ደረጃ ለማጠናከር የኢትዮጵያ መንግስት በኢስላላባድ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኑን ነው ያስታወቁት።

ከዚህ ባለፈም በትላንትናው ዕለት ሃይል ማመንጨት የጀመረውን ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህም አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ፍትሐዊና ተገቢ በሆነ መንገድ እንዲሁም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን በማይጎዳ መልኩ በግድቡ የልማት ስራዎችን እያከናወነች መሆኗን ገልጸዋል።

 
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.