Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን በ10 ወራት ውስጥ ብቻ ድርቁ 5 ቢሊየን ብር የሚገመት ጉዳት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን ባለፉት ሶስት ወራት ከሚያስፈልገው የከብቶች መኖ ማቅረብ የተቻለው 5 በመቶ ያህል ብቻ መሆኑን የዞኑ አደጋ ስጋት መከላከልና የልማት ተነሺዎች ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
 
የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ጉዮ ጨርፊ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷6 ነጥብ 8 ሚሊየን ከሚገመተው የእንስሳት ሃብት ውስጥ 10 በመቶ ያህሉን ለማትረፍ እየተሰራ ነው።
 
ለዚህም ከብቶች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወሩ ከማድረግ ባለፈ መኖና ውሃ ለማቅረብ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ባለፉት ሶስት ወራት ከ5 ሚሊየን በላይ የእንስሳት መኖ ያስፈልግ እንደነበር የጠቆሙት ሃላፊው ÷ ይሁን እንጅ ማቅረብ የተቻለው 5 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው ብለዋል።
 
ይህ ሁኔታም በድርቁ የተጠቁ እንስሳትን ለማትረፍ አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የተናገሩት።
 
በዞኑ በተፈጠረው ድርቅ ሳቢያ ባለፉት አስር ወራት ውስጥ 5 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ማድረሱን አመላክተዋል፡፡
 
በሌላ በኩል በተከሰተው ድርቅ ከ707 ሺህ በላይ ዜጎች የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልጸው÷ ከእነዚህ ውስጥም 524 ሺህ ያህሉ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.