Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የተለያዩ አገራት ገንዘቦችን አስመስለው በማተም የተጠረጠሩ ካሜሩናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የተለያዩ አገራት ገንዘቦችን አስመስለው ሲያትሙ ተገኝተዋል የተባሉ ካሜሩናውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ገለጸ፡፡

ፖሊስ እንዳለው፥ ግለሰቦቹ በወረዳው በተለምዶ ፕሬሰዴንሽያል ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ሲያትሟቸው ከነበሩ ልዩ ልዩ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች እና ከተለያዩ የኬሚካል ቁሳቁሶች ጋር ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

የአከባቢው ህብረተሰብ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ብርቱ ክትትል ሐሰተኛ ኖቶቹን ሲያመርቱ የነበሩ ሁለት የካሜሩን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦችም የካቲት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ግለሰቦቹ የአሜሪካ ዶላር፣ የሱዳን፣ የቻይና እና የማይናማር እንዲሁም የታንዛኒያ ገንዘቦችን አስመስለው ሲያትሙ እንደነበር መማላከቱን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.