የሀገር ውስጥ ዜና

በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖም ኢኮኖሚው እድገት አስመዝግቧል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

By Feven Bishaw

February 22, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖም ኢኮኖሚው እድገት አስመዝግቧል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በምላሻቸው በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖም ኢኮኖሚው እድገት አስመዝግቧል ነው ያሉት፡፡