Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተደርገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የተመድ የካፒታል ልማት ፈንድ እና የአለም አቀፉ የቢዝነስ ማሽን ኮርፖሬሽን የሴቶችና ወጣቶችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ በኦንላይን ትምህርት መስክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ሴቶችና ወጣቶች የራሳቸውን የቴክኖሎጂ መፍትሄ እንዲያፈልቁ፣ እንዲያሳድጉና ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩት ለማስቻል ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ የዜጎችን የዲጂታል እውቀት ማሳደግ ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የዜጎችን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝነት አለው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ ስምምነቱ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

የአለም አቀፉ የቢዝነስ ማሽን ኮርፖሬሽን የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ የዲጂታል እውቀት ተነሳሽነት መሪ ኦሪየት ናየል በአፍሪካ ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ለኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን እንዲሁም ለቴክኖሎጂ አልሚዎች ስልጠናዎች እየሰጡ መሆኑን አብራርተዋል።

የአፍሪካ መዳረሻ በሆነችው ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት ማድረጋችን ለአፍሪካ ትልቅ አቅም ይፈጥራልም ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካፒታል ልማት ፈንድ የፕሮጀክት መሪ አቶ እንዳሻው ተስፋዬ፥ “የዲጂታል ኔሽን አፍሪካ” የሚል ተነሳሽነት በመመስረት የአፍሪካውያንን የዲጂታል እውቀት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ትምህርቱ በክላውድ አገልግሎት፣ በአዲሱ ቴክኖሎጂ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በዴታ ሳይንስ እና በኢንተርኔት ቁሶች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ሲሆን፥ የኢንደስትሪ ተኮር ስልጠናዎችን እንደሚያካትትም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.