Fana: At a Speed of Life!

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በ+2517 ኮድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ አሥር ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ1 ነጥብ 5ሚሊየን ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት መዕዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱበት በኢትዮጵያ አዲስ ጅማሮ የሆነው የቴሌኮም ዘርፍ ላይ ኢትዮጵያዊያንን የሚመጥን ዘመናዊ የኔትዎርክ ዝርጋታ እንደሚያካሂድ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ሃላፊ ማቲው ሀሪሰን ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በአዳማ በመቶ ሚሊየን ዶላር ወጪ የዳታ ማዕከል መገንባቱን ያነሱት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ክፍል ዋና ሃላፊ ፔድሮ ራቫካል በዚህ ዓመት በሁለቱም ከተሞች ሁለት ተጨማሪ የዳታ ማዕከል እንደሚገነቡ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ አሥር ዓመታት 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በማፍሰስም የዘርፉን ተጠቃሚነት የማሻሻል ዕቅድ እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በ (+2517) ኮድ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ነው የተባለው፡፡

በሜሮን ሙሉጌታ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.