Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ውይይት አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ውይይት በማድረግ ለጨፌ ኦሮሚያ መምራቱን የክልሉ የመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮ ሀላፊው አቶ ሀይሉ አዱኛ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የክልሉ አስተዳደር ምክር ቤት አራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ውይይት በማድረግ ወደ ጨፌ ኦሮሚያ መርቷል ብለዋል።

በዚህም መሰረት የህዝብ ሰላም አደረጃጀት ‘ጋቸነ ሲርና’ ህጋዊ ማዕቀፍ አግኝቶ እንዲንቀሳቀስ ለማስቻል ወሳኝ በመሆኑ ወደ ክልሉ ጨፌ መመራቱን ተናግረዋል።

የክልሉ ነዋሪዎች የመደጋገፍ ባህል ኢኮኖሚውን ሊያሳድግ የሚችል ‘ጋዲሰ ቡሳ ጎኖፋ’ የኦሮሚያ አደጋ ስጋትና የልማት ተነሺዎች ኮሚሽን ተብሎ የሚታወቀውን የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ መምራቱን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የመንግስት የልማት ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ላይ የክልሉ አስተዳር ም/ቤት ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ ይህም የክልሉን የልማት ድርጅቶች አፈፃፀም ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል ረቂቅ አዋጅ መሆኑን አብራርተዋል ።

በክልሉ የተጀመሩ 73 የሚደርሱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚውል 13 ነጥብ 95 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀድቅም ምክር ቤቱ በመወያየት ለጨፌው መምራቱን አቶ ሀይሉ አስረድተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.