Fana: At a Speed of Life!

የአፍሮኮም ልዑካን ቡድን የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩስያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትሥሥር ማስቀጠል እና ማስተዋወቅ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው የአፍሮኮም ልዑካን ቡድን ቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የአፍሮኮም የጤና እንክብካቤና ፋርማሲቲዩካል ምክትል ፕሬዚዳንት ሞሮዞቫ ኦልጋ እንዲሁም ሌሎች የተቋሙ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የልዑካን ቡድኑ የቦሌ ለሚ እና የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከተ ሲሆን÷ በፓርኮቹ ስራ አስኪያጆች በኩል ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡

ልዑኩ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳንዶካን ደበበ እና ከኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽፈራው ሶሎሞን ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ ኢትዮጵያ ከሩስያ ጋር ያላትን የቆየ ወዳጅነት ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና የሥራ ሂደት ላይ በጋራ መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ገንቢ ሀሳቦች አንስተዋል፡፡

ስለተደረገላቸው አቀባበልና ማብራሪያ ያመሰገኑት ምክትል ፕሬዝዳንቷ ሞሮዞቫ ኦልጋ ÷ አፍሮኮም ከኢትዮጵያ በተለይም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በትብብር መሥራት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ እንደሚሰሩ ገልጸው ፣ ከጉብኝቱም በርካታ ግብዓቶች ማግኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

አፍሮኮም ሩስያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትሥሥር ማስጠበቅ ብሎም ማስተዋወቅ ላይ ለመስራት በፈረንጆቹ በ2019 የተቋቋመ ተቋም ሲሆን በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሚሰሩ ኩባንያዎችና ወደ ሩስያ ገበያ መግባት የሚፈልጉ ድርጅቶችን አባል አድርጎ የሚንቀሳቀስ ተቋም መሆኑን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.