Fana: At a Speed of Life!

በጫማ ውስጥ በመደበቅ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ ሁለት ኪ.ግ ወርቅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኤርፖርት በገቢ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የታቀደ ሁለት ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

በጫማ ውስጥ በመደበቅ በገቢ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የታቀደው ሁለት ኪሎ ግራም የሚመዝነው ወርቅ ግምታዊ ዋጋው 6 ሚሊየን 600 ሺህ ብር መሆኑ ተገልጿል።

የጉምሩክ ኮሚሽን እንደገለጸው፥ ወርቁን በጫማ ውስጥ በመደበቅ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተደረገው የረቀቀ ሙከራ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደህንነት እና ኮንትሮባንድ ክትትል ነው የተያዘው።

የወንጀሉ ሁኔታ በመጣራት ሂደት ላይ እንደሚገኝም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.