ስፓርት

የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን የመሩት ረዳት ዳኛ ከውድድሩ ተሰናበቱ

By Feven Bishaw

February 23, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን የመሩት ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ ከውድድሩ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

በተጠናቀቀው የ13ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ ላይ ረዳት ዳኛው ባሳዩት የዳኝነት ስህተት ነው ቅጣቱ የተላለፈባቸው፡፡

በዕለቱ ወልቂጤ ከተማ በመጀመሪያው አጋማሽ በአማካዩ በሀይሉ ተሻገር አማካኝነት ግብ ያስቆጠረ ቢሆንም÷ ረዳት ዳኛ ኳሱ ከጫዋታ ውጭ ነዉ ማለታቸውን ተከትሎ ጎሉ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡

ይሁን እንጂ ጎሉ ከጨዋታ ውጭ አለመሆኑ በዳኞች ኮሚቴ ከተረጋገጠ በኋላ ኮሚቴዉ የዕለቱ ረዳት ዳኛ ዳንኤል ጥበቡ በፈፀሙት የዳኝነት ስህትት ከውድድሩ በማገድ ከድሬዳዋ አሰናብቷቸዋል፡፡