የአዲስ -ጊቤ ወንዝ ዋና መንገድ ጥገና ስራ በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ ሊገነባ ነው
አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ – ጊቤ ወንዝ ዋና መንገድ በ1 ነጥብ 47 ቢሊየን ብር ወጪ የከባድ ጥገና ስራ ሊካሄድለት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍሰትን የሚያስተናግደው ይህ መንገድ ÷ ካለው ጉልህ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ጥገናውን ማድረግ ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡
64 ኪሜ የሚረዝመው የአዲስ -ጊቤ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አካል የሆነው ከአዲስ – ቆራ የሚዘልቀው መንገድ ከፍተኛ ጥገናን ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ግንባታውን የሚሰራው የስራ ተቋራጭ ቤአይካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን÷ ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ያከናውናል፡፡
ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚውለው 1ነጥብ 47 ቢሊየን ብር ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ከቆራ -ጊቤ ወንዝ 93 ኪሜ ከፍተኛ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክት ለመገንባትም በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ ለግንባታው የሚውለውን 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገንዘብ ከመንግስት በጀት ወጪ የሚደረግበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የመንገዱ ጥገና አሽከርካሪና ተሳፋሪዎች እንግልት በማስቀረት የትራንስፖርት ምልልሱን ምቹና የተቀላጠፈ እንዲሆንና በጉዞ ወቅት የሚያጋጥም የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ያስችላል መባሉን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!