Fana: At a Speed of Life!

በወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤንነት ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጣቶችንና የአፍላ ወጣቶችን ጤንነት ለማሻሻል የሚመለከታቸው አካላት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት የወጣቶችንና የአፍላ ወጣቶችን ጤና በሚመለከት የ5 ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።

ሁለተኛው የጤና ዘርፍ ዕቅድ የወጣቶችንና የአፍላ ወጣቶችን ጤና በዕቅድ ውስጥ ተካተው ከሚተገበሩ የጤና ዕቅዶች መካከል አንዱና ዋናው እንደሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ ጠቅሰዋል፡፡

በወጣቶችና በአፍላ ወጣቶች ዙሪያ መስራት ከጤናዉ በተጨማሪ በሀገር ደረጃ የራሱ የሆነ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የተናገሩት፡፡

የወጣቶችንና የአፍላ ወጣቶችን ጉዳይ የሚመለከታቸዉ አካላት በተበታተነ ሁኔታ የሚያከናውኑትን ተግባር በአንድ ማዕከል በማድረግ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚኖርባቸውም አመላክተዋል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙትን ወጣቶችንና አፍላ ወጣቶችን በጤናው ዘርፍ የላቀ ተጠቃሚ ለማድረግ ከጎናቸው መቆም እንደሚገባ ያሳሰቡት ደግሞ በሚኒስቴሩ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና ቴክኒካል አማካሪ አቶ እዮብ ጌታቸው ናቸው፡፡

በጤናው ዘርፍ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ሚና መጠናከር እንዳለበት ገልጸው÷ የሁሉም ተቋማት ጉዳይ በመሆኑ በትብብር መስራት እንደሚጠበቅም አንስተዋል፡፡

በውይይቱ የክልል ጤና ቢሮ፣ የዞን ጤና መምሪያ፣ ከወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት፣ የማህበረሰብ ተወካዮች፣ ከእምነት ተቋማት የተውጣጡ እንዲሁም የሚመለከታቸው አጋር አካላት መሳተፋቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመልከታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.