የሀገር ውስጥ ዜና

በዳባት በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ተጠልለው የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ወደ አለም ዋጭ መጠለያ ካምፕ ተዛወሩ

By Alemayehu Geremew

February 23, 2022

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ዳባት ከተማ በህዝብ መገልገያ ቦታዎች ተጠልለው የነበሩ 1 ሺህ 400 የኤርትራ ስደተኞች ወደ አለም ዋጭ የመጠለያ ካምፕ መዛወራቸው ተገለጸ፡፡

ስደተኞቹ ከሐምሌ 13 ቀን 2021 ዓ.ም. ጀምሮ በዳባት ከተማ በሦስት የህዝብ መገልገያ ቦታዎች ተጠልለው እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዝውውሩ ስነ ስርዓት ላይ የሰሜን ጎንደር ዞንና ዳባት ከተማ አስተዳዳሪዎች፣ የዓለማቀፍ የስደተኞች ኮሚሽን ና የሌሎች ዓለማቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።