Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነትን ተቋማዊ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነትን ተቋማዊ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን በመተባበር በፌደራልና በክልል መንግስታት ግንኙነትና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረና ሕጋዊ ማዕቀፎቹን በማዘጋጀት ለውይይት ማቅረብን ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ዛህራ ሁመድ እንደገለፁት፥ እውነተኛ ኅብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝምን እውን ለማድረግ “የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት ተቋማዊ ሊሆን ይገባል።

ባለፉት 27 ዓመታት በፌዴራልና በክልሎች መንግስታት መካከል የነበረው ግንኙነት ተገቢው ቦታ ያልተሰጠው፣ ሕግና አሰራርን ያልተከተለና ከፌዴራል ስርዓት መርሆዎችና እሴቶች ፍፁም ተቃራኒ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ምክንያትም እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓት ሳይተገበር ቆይቷል ነው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ።

የመንግስታት ግንኙነቱን ተቋማዊ ለማድረግ ምክር ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸው÷ ለተግባራዊነቱ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎችን ለማበጀት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በተለይም የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነትን ለማጠናከር የተቋቋሙ ፎረሞች ወደ ስራ እንዲገቡ ጭምር እየተሰራ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

የፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ደሳ ቡልቻ በበኩላቸው፥ የፌዴራል ስርዓቱ እንዲጠናከር ከፌዴሬሽኑ ጋር በትብብር እየሰራን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.