በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ እና በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ ነው- አምባሳደር መለስ አለም
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ እና በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ ነው ሲሉ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ አለም ተናገሩ፡፡
አምበሳደር መለስ በኬንያ የሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችል አገር አቀፍ ዘመቻ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ በብዙ ፈተና ውስጥ ያለፈውን የአገራቱን ጠንካራ ወዳጅነት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለው ግንኙነት ታሪካዊ እና በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባ መሆኑን አመልክተው፥ ይህም የሁለቱ አገራት የተለያየ ትውልድ መሪዎች የመሠረቱት መሆኑን ጠቅሰዋል።
አምባሳደሩ ኬንያ በምስራቅ አፍሪካ በዴሞክራሲ፣ በሰላም እና መረጋጋት አርዓያ ሆና የምትጠቀስ አገር መሆኗን በመጠቆም የኬንያ ሰላም መረጋጋት እና ብልፅግና የኢትዮጵያም ጭምር ነው ሲሉ አብራርተዋል ።
ቀጣዩ የኬንያ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ መመኘታቸውንም በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!