Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካና ሩሲያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እና የሩስያ የኢኮኖሚ ትብብር ማስተባበሪያ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት (አፍሮኮም) ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፈተ፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርአቱ ላይ የሩሲያ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ሴናተር ኢጎር ሞሮዞቭ፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረሂን እና የሃይማኖት አባቶችን የወከሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የበላይ ሃላፊ ብጹዕ አቡነ አረጋዊ እና የመንግስት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሴናተር ኢጎር እንዳሉት፥ ማዕከሉ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በንግድ እና በኢንቨስትመንት እና በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች ለሚያደርጉት ግንኙነት የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

አምባሳደር ኤቭጀኒ ተረሒን በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሁለትዮሽ ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ ግንኙነት ቢኖራቸውም በንግዱና በኢኮኖሚው ዘርፍ የጎላ ትስስር ሳይፈጥሩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል።

የጽህፈት ቤቱ መከፈትም አገራቱ ለሚያደርጉት የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር የመሰረት ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ነው ያሉት።

በወንድወሰን አረጋኸኝ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.