Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎድ አካባቢዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ5 ሚሊየን ብር የምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡
በጅግጅጋ ከተማ በመገኘት ድጋፋን ያስረከቡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢንጂር ሀብታሙ ኢተፋ ፥ የተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡
ከደረሰው ጉዳት አንፃር ሚኒስቴር መ/ቤቱ ያደረገው ድጋፍ በቂ ሆኖ ሳይሆን ጉዳታችሁ ጉዳታችን መሆኑን ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በርካታ የውሃ ፕሮጀክቶች ወደስራ ይገባሉ ያሉት ሚኒስትሩ ፥ በዋናነት ችግሩን ለመፍታት ሰፋፊ የውሃ ፕሮጀክቶች አስፈላጊ ስለመሆናቸው ነው የተናገሩት፡፡
ድጋፋን የተረከቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ሁሴን ቃሲም ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ፥ የተጀመሩ ስራዎች ለፍሬ እንዲበቁ ክልሉ ሌት ተቀን እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.