Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሩስያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የነበሯቸውን ትብብሮችና ውሎች ለማደስና ለመተግበር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ከሩስያ ፌዴሬሽን ፓርላማ ሴናተር ኢጎር መሮዞቭ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያዩ።

በውይይታቸውም ከአንድ ምዕተ ዓመት ተኩል በላይ የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ማስቀጠል እንደሚገባ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የሩስያ ፌደሬሽን ሴናተር ኢጎር መሮዞቭ በበኩላቸው ፥ ሀገራቸው በጠፈር ቴክኖሎጂ፣ በቴክኖሎጂያዊ ከተማ ግንባታ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ ያላትን የካበተ ልምድ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አስረድተዋል፡፡

ሴናተሩ ኒውክሌርን ለሠላማዊ አገልግሎቶች ማበልጸግ እና መጠቀም እንደሚቻልም ገልጸው ፥ በዘርፉ ላይ ያላቸውን ዕውቀትም ማካፈል እንደሚፈልጉ ነው የጠቆሙት፡፡

በተጨማሪም ሩስያ በፋርማሲ ቴክኖሎጂ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች የሁለትዮሽ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ ያላትን አቅም ለማካፈልና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት መንግስታቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል።

የግሎናስ ዓለም አቀፍ ጂፒኤስ አገልግሎትም በሩስያ ከተሞች ሁሉ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዳረስ የነበረውን አበርክቶ አስረድተዋል።

ሴናተር ኢጎር፥ ዶክተር በለጠ ሞላና አመራራቸው ሞስኮ በመገኘት የልምድ ልውውጥ ጉብኝት እንዲያደርጉም ጋብዘዋል።

በተጨማሪ በቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ በመጪው ሰኔ የሚካሄደው ዓለማቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ሚኒስትሩ እንዲገኙ እንዲገኙም ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የሩስያ ፌደሬሽን አምባሳደር ኢቭኒ ተርኪያን ፥ ኢትዮጵያና ሩስያ በስማርት ሲቲ ፕሮጀክት፣ በጸጥታና ደኅንነት እንዲሁም በትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ ተግባራትን በአጭር ጊዜ አስቀምጠን ወደ ሥራ እናስገባለን ብለዋል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ስምምነት ላይ የተደረሱ ውሎችን ለማደስ እና ቀጣይ ግንኙነቶችን እና የትብብር ማዕቀፎችንም ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን በመለየት ወደ ተጨባጭ እንቅስቃሴ ለመግባትም ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስቴሩ በመረጃው አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.