በልደታ ክ/ከተማ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 4 አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ አራት አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ፓሊስ መምሪያና በማህበርሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት ከአዲሱ የአመራር ምደባ በፊት የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፋይናንስ አስተዳደር ፑል ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ እንዲሁም በፑሉ የግዥ ቡድን መሪና የግዥ ባለሙያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር የደረሰበትን ሁኔታ በየጊዜው ለህዝቡ እንደሚያሳውቅ በመግለጽ፥ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በቁርጠኝነት እንደሚታገል አስታውቋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!